Jump to content

User:Servant of God Mintesnot BC

From Wikipedia, the free encyclopedia

ወንጌል የሚለው ቃል በግሪክ እቫንጄሊዮን በመባል የሚታወቅ ሲሆን ትርጉሙም መልካም ዜና : የምስራች ቃል ማለት ነው።

ድልን የሚያውጅ : ለልብ ደስታን የሚሰጥ መልዕክት ማለት ነው።

ወንጌል የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውሰጥ ከ98 በላይ ተጽፎ ይገኛል።

ወንጌል => በኀጢአት ምክንያት ከ እግዚአብሔር ተለይቶ የነበረው ሰው እግዚአብሔር የራሱ መፍትሔ መንገድ አዘጋጅቶ ወደ እራሱ ህብረት ለመመለስ ለ አዳምና ለሔዋን : ከዚያም ለአብርሃም : እንዲሁም ለእስራኤላውያን የገባውን ቃል ኪዳን በመሲሁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ በመፈጸም የዘላለም ሕይወት መንገድ ለሰዎች ሁሉ የከፈተበት የምስራች የሚያበስር ነው።

ወንጌል በአዲስ ኪዳን ብቻ የተገለጠ መልዕክት ሳይሆን የብሉ ኪዳን ቁልፍ መልዕክት ነው። መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ማንነት ተጠራጥሮ መልዕክተኞች ወደ ኢየሱስ በላከበት ጊዜ ኢየሱስ ስለራሱና ስለ መልዕክቱ የገለጠው ይህን እውነት ነበር።

ይህም መልዕክት የብሉ ኪዳን መካከለኛ መልዕክት ወንጌል እንደነበር (ማቲ 11:2-5) የሚገልጽ ነው። ነቢዩ ኢሳያስም በትንቢቱ የተናገረው ስለዚህ ወንጌል እንደነበር ኢየሱስ ራሱ በምድር ላይ አገልግሎት በጀመረበት ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ:-

"የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል "

(ሉቃ 4: 17-19)