Jump to content

User:Gebrewahd kinfe

From Wikipedia, the free encyclopedia

"...መሬትና እዩ ራያ ምስ ቆቦ ፥

ወልቃይት ፀገደ ጎቦ ዝኸቦቦ..."

➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ክፍል - ፪ [ስለ ራያና ቆቦ]

ከኣንኳር የወቅቱ ታሪክ ለመንደርደር ያክል የኣፄ ዮሃንስ ፬ኛ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት የልእልት ወለተ እስራኤል ስዮም መንገሻ ባለቤት ደጃዝማች ገ/ስላሴ እንዳረፉ የኣፄ ኃ/ስላሴ ልጅ ለሆነው ለኣልጋወራሽ ኣስፋወሰን በ1948 ዓ/ም ይዳራሉ [Political Marriage መሆኑ ነው]። ኣልጋወራሹ በወቅቱ የወሎ ጠቅላይ ግዛት ኣስተዳዳሪ ነበሩ፡፡ እንደ ጥሎሽም ቆቦንና ኣንላማጣን ከትግራይ ጠቅላይ ግዛት ወደ ወሎ ጠቅላይ ግዛት እንዲዛወር ሆነ። በዚያን ወቅት የትግራይ ጠቅላይ ግዛት ገዢ ለነበሩት ለልኡል ስዩም መንገሻ [የሙሽሪት ወላጅ] ከትግራይ ገዚዎች ጥያቄ ያነሱት ደጃዝማች ለምለም ዓጋመ ሲሆኑ "...መሬታችን ወደ ወሎ ሄደ ፤ የተደረገው ነገር ልክ ኣይደለም..." ብለው ቅሬታቸውን ኣስሰምተው ነበር።

ይህ በሆነ ባመቱ በትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር የትግሬ ጠቅላይ ግዛት ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት ሓምለ 26/1949 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ "...ቀደም ሲል ከትግራይ ጠቅላይ ግዛት ቆቦና ኣላማጣ የሚባሉ ኣገሮች ተቆርሰው ወደ ወሎ ጠቅላይ ግዛት በመዛወራቸው ምክንያት ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር የነበረው ገቢያችን ወደ ኣንድ መቶ ሰባ ሺህ ብር ሆኖ ባሳየው ከፍተኛ ቅናሽ ወጭያችንን ሳያስችለን መቅረቱ ግልፅ ነው..." ብለው ከመቐለ ለማእከላዊው መንግስት ያቀረቡበት የኣቤቱታ ሰነድ ከታች መመልከቱ ድንቅ ነው።

ልዑል መንገሻ ስዩም ስለነኚህ የትግራይ ሉዓላዊ ግዛትነት የዛሬ 5 ዓመት ገደማ በተናገሩት ምስክርነት ኣፄ ሃይለስላሴ በ1948 ዓ/ም ወልቃይትንና ፀገዴን ከምዕራብ ትግራይ ቆርሰው በደጃዝማች ብሩ ይተዳደሩ ዘንድ ወደ ጎንደር [በጌምድር] እንዳካለሏቸውና ራያንና ቆቦን ደግሞ ከትግራይ ወደ ወሎ እንዲካለሉ ማድረጋቸውን #Rev.Michael_Russell ካስቀመጠው ተጨባጭ እውነታ በተጨማሪ ከታች ያሉትን የወቅቱ ታሪካዊ ሰነዶችን ማጤኑ ይበጃል።

ንጉሱ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ማለትም በ1949 ዓ/ም የተፃፈው ይሄው ታሪካዊ ሰነድ ቆቦ እና ኣላማጣ ከዚሁ ዘመን በፊት ማለትም ከ1949 ዓ/ም በፊት የትግራይ ግዛት እንደነበሩና ንጉሱ እነዚህን ግዛቶች ከደቡብ ትግራይ ቆርሰው በጥሎሽ መልክ ወደ ወሎ ማካለላቸውን ሰነዱ ይመሰክራል። በኣከባቢው መምህራንን ስለመቅጠር ኣስመልክቶ በወቅቱ የተፃፈው ደብዳቤ ቃል በቃል እንደሚከተለው ይላል ፦

<< ...ቁጥር 3101/36 ሓምሌ 26 ቀን ፲፱፻፵፱ [1949] ዓ/ም

የትምህርትና ስነጥበብ ሚኒስቴር ፥ የትግሬ ጠቅላይ ግዛት ትምህርት ቤቶች ጽሕፈት ቤት ፥

ጉዳዩ ፦ ስለ ኣዲስ መምህራን ፦

ለክቡር የትምህርትና ስነ ጥበብ ሚንስትር ፥ ኣዲስ ኣበባ ፥

ክቡር ሆይ ፦

የጠቅላይ ግዛቱ የትምህርት ታክስ ገቢያችን በደብሮችና እንዲሁም በራያና ኣዘቦ ግዛት የሚገኘው ቆቦና ኣላማጣ የሚባሉ ኣገሮች ተቆርጠው ወደ ወሎ ጠቅላይ ግዛት በመዛወራቸው ምክንያት ሁለት መቶ ኣምሳ ሺህ ብር የነበረው ገቢያችን ወደ ኣንድ መቶ ሰባ ሺህ ብር ሆኖ ባሳየው ከፍተኛ ቅናሽ ወጪኣቸውን ሳያስችለን መቅረቱን ግልፅ ነው። በዚሁ ምክንያት ያሁኑ ገቢያችን ከወጪያችን ጋር በማመዛዘን ኣለን ብለን የምንተማመነው ገንዘባችን ለመምህራንና ሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ ከነሓሴ ወር /1949 ዓ/ም የሚያልፍ ገንዘብ እንደሌለን በመግለፅ ለ1950 ዓ/ም ኣዲስ መምህራን የማያስፈልጉ መሆኑን ለክቡርነትዎ ሰኔ 13/1949 ዓ/ም በቁጥር 2679/32 በተፃፈ ደብዳቤኣችን ኣመልክተን ነበር። ነገር ግን በዚሁ ዓመት ከመምህራን ማሰልጠኛ ከወጠለት ኣስር መምህራን ተመድበው ስለተላኩልን በገንዘባችን ምክንያት ስለደመወዛቸው ኣከፋፈል ከባድ ሸክም ሆኖብን ይታያል። ስለሆነ ግን ክቡርነትዎ የተላኩት መምህራን እንዲመለሱ ማድረግ የበላይን ትእዛዝ መቃወም እንዳያስመስልብን ተቀብለናቸዋል።

እነዚህ ኣዲሶችን መምህራን ለመመደብ ባለፈው ጉባኤ እንደተገለፀው ት/ት ቤቶች በጣም የተስፋፉ ከመሆናቸውም በላይ በቂ መምህራን ስላሏቸው ኣዲስ ተቀጣሪዎችን ስራ ከማስፈታት ይልቅ በታህሳስ ወር 1949 ዓ/ም የጠቅላይ ግዛቱ የት/ት ቦርድ ተሰብስቦ በጠቅላይ ግዛቱ በሁለት ቦታ ላይ ትም/...>> ይላል።

በዚህ ታሪካዊ ደብዳቤ "... በራያና ኣዘቦ ግዛት የሚገኘው ቆቦና ኣላማጣ የሚባሉ ኣገሮች ተቆርጠው ወደ ወሎ ጠቅላይ ግዛት በመዛወራቸው ምክንያት..." የሚለውን ነጥብ ስለ ራያ ቆቦ ማንነት በግልፅ ይናገራል። በስተ ደቡብ የትግራይ ድንበር ኣሉውሃ ወንዝ መሆኑን ያስረግጣል። ይህ ኢህኣዴግ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ ከግንቦት1983 ዓ/ም በፊት እስከ 1947 ዓ/ም መሬት ላይ የነበረ ሃቅ ነው። ራያ መቼም ቢሆን ኣማራ ሆኖ ኣያውቅም ፤ ለወደፊትም ኣይሆንም። ምክንያቱ ደግሞ ገና ከጅምሩ እንዲያ ስላልሆነ። የራያ ቆቦ ህዝብ ትግራዋይ ህዝብ ነው። ከዚያ ቢዘገይም የ16ኛው መ/ክ/ዘ የግራኝ ኣሕመድ ወረራን ተከትሎ በተፈጠረው የኢምንት መዛነቅ ራያ ቆቦ በጥቂቱ ኦሮሞ ቢሆን ነው። ከዚህ ውጭ ከ98% በላይ ራያ ቆቦ በየትኛውም የማንነትም የታሪክም መስፈርት ኣማራ እሚሆንበት ዕድል የለም። ራያ ቆቦ ከኣማራነት ቀድሞ በትግራዋይነት ትግራዋይ ሆኖ ፀንቶ የኖረ ህዝብ ነው። "የአማራ" የሚባል ነገር የተፈጠረው ትናንት በኢህኣዲግ በ1983 ዓ/ም የማባባያ ፖለቲካ ዘመን ነው። ለዚሁ ማረጋገጫችን ከስር ያለውን የታሪክ ሰነዶች ማመሰካከር በቂ ነው። እልፍ ካለም የቆቦ ፥ የመንደፈራ ፥ የራማ እና የዞብል ኗሪዎችን ማንነት ፥ ኣያት ቅድመ ኣያት ጠይቆ ማረጋገጥ ነው። የትግራይ ድንበር በስተ ደቡብ ኣልውሃ ምላሽ ነው። ታድያ እነ #Habtamu_Ayalew ፥ #Achamyeleh_Tamiru የመሳሰሉ የኣማራ መርጦ ኣልቃሽ #Act_Beasts ኣለርጂ ስለሚሆንባቸው ይህንን ታሪካዊ ሰነድ ማየትም መነካካትም ኣይፈልጉም።

ክፍል - ፫ ይቀጥላል...

[ወዓካፃ ፥ ፮ ሕዳር ፳፻፲፭ ዓ.ግ ፥ መቐለ ፥ ሃገረ ትግራይ]