User:Andiyoo12
አርሲ ሮቤ ከተማ የከተማዋ ስያሜ መነሻው ሶስት መሰረታዊ ሀሳቦች ናቸው ፡፡ እነሱም፡- 1) አንድ በአከባቢው ሲኖሩ የነበሩ አቶ ሮባ የሚባሉ አዛውንት በቦታው ይኖሩ ስለነበር ከአዛውንቱ ስም በመነሳት ሮባ ከሚለው ስም ሮቤ ተባለች ፣ 2) በድሮው ወቅት በአከባቢው ከባድ ዝናብ ይዘንብ ስለነበር ሮባ/ዝናብ/ ከሚለው ኦሮምኛ ቃል ሮቤ እንደተባለች እንዲሁም 3) ሮቤ የሚባል ወንዝ ከተማዋን አsርት ስለሚያልፍ ከወንዙ ስያሜ በመነሳት ሮቤ ተባለች ይባላል :: አርሲ ሮቤ ከተማ የተመሰረተችው በ1914 ዓ.ም ሲሆን ህጋዊ እውቅና ያገኘችው ደግሞ በ1945 ዓ.ም ነው፡፡ የከተማው የህዝብ ብዛት ወንድ 22,964 ሴት 19,876 ድምር 42,840 ሲሆን በ 2 ቀበሌ በ 10 ዞን በ 285 የቡድን ሰራዊት እና በ1443 የልማት ሰራዊት ተደራጅቶ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በመሰረተ ልማትና የከተማ ገጽታ ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል ፡፡ ከተማዋ የምትገኘው በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በ7050'11.33- 7053'35.98 ሰሜን ኬንትሮስ እና 39036'43.37- 39038'57.02 ምስራቅ ኬንትሮስ መሃል ከሀገሪትዋ መዲና ከተማ አዲስ አበባ 183 ኪ.ሜ ከአረሲ ዞን አሰላ ከተማ 98 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንዲሁም ከባህር ጠለል በላይ 2423 ሜትር ከፍታ ላይ ነው፡፡ የከተማዋ የሙቀት መጠን በአማካይ ከ 13.3-20.6 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን የዝናብ መጠን ደግሞ በአማካይ 780.30-1129.8 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
የከተማው ራዕይ፡-
በ 2012 ዓ.ም በአርሲ ሮቤ ከተማ ውስጥ የከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ተስፋፍቶ ፤ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የአሰሪና ሰራተኞች ህግ ተከብሮ፤ የማህበረሰቡ አር ተሻሽሎ ወደ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ከተሞች እንዲያድግ ማድረግ ነው፡፡
1) የከተማው ልዩ መገለጫ ፡-
ከተማዋ ለሰባት ወረዳዎች እና ለ አስራ አምስት አጎራባች ሰባት ወረዳዎች ውስጥ ላሉ ከተማዎች እንዲሁም ለባሌ ዞን መተላለፊያ እና አምስት መግቢያና መውጫ በሮች ያሉዋት መሆንዋ ፤
ሁለት በጋ ከክረምት የማያቁዋርጡ ወንዞች ያሉዋት ወይም ከተማዋን አቁዋርጠው የሚያልፉ መሆናቸው ፤
ከተማዋ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች እንደ ኦሮሞ ፣ አማራ ፣ ስልጤ ፣ ጉራጌ ፣ ትግሬ ፣ ወላይታ እና ወዘተ መኖሪያ መሆንዋ ፤
ከተማዋ በወይናደጋ እና ለህዝቦችዋ መኖሪያ ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት ባለበት ቦታ ላይ የተመሰረተች መሆንዋ ፤
የከተማዋ መልካም ምድራዊ አቀማመጥ ለወደፊት በሁሉም አቅጣጫ ለማደግ የሚችል እንዲሁም ከተማው ውብ ፤ ጽዱ እና በደን የተሸፈነ /የለማ/ መሆኑ፤
ከተማዋ የጤፍ እና ስንዴ አምራች ወረዳ ዋና ከተማ መሆንዋ ፤
ከተማዋ መሰረተ ልማት እንደ የ 24 ሰአት መብራት ፣ ውሃ ፣ የጠጠርና ኮብልስቶን መንገድ ፣ ተንቀሳቃሽ እና መደበኛ ስልክ ተቁዋማት የተሙዋሉላት መሆንዋ ፤
ከተማዋ ማህበራዊ ተቁዋማት የመንግስት ሆስፒታል ፣ ጤና ጣቢያ ፣ ጤና ኬላዎች ፣ ሁለት አንደኛ ደረጃ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤቶች እና የመሰናዶ ትምርት ቤቶች እንዲሁም የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ፣ ማረሚያ ቤት እና የእንሰሳት ህክምና ፤ የግል ደግሞ የሶስት ዩኒቨርስቲ ቅርንጫፍ ፣ አራት አፀደ ህጻናት ፣ አስራ አራት መካከለኛና መለስተኛ ክሊኒክ እና ስምንት ፋርማሲዎች ፣ ያሉዋት መሆንዋ ፤
የፋይናንስና ኢኮኖሚክ ተsማት በተመለከተ ሁለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ፣ አሮሚያ ኢንተርናሽናል እና ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እንዲሁም አዋሽ ባንክ ፤ በተጨማሪም ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ማህበር ፣ ወሳሳ ፣ መክሊት እና መተማመን የማይክሮ ፋይናንስ ተsማት ያሉዋት መሆንዋ እና የመሳሰሉት ናቸው ::
2. የከተማ የልማታዊ አመራር አቅም ግንባታ ስራዎች
በከተማው 1443 የለውጥ ሰራዊት በማደራጀት በተለያየ አጫጭር ስልጠናዎች እና ማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶች ፣ በስራ ላይ ግምገማ እና በድረመልስ ማበረታቻ እውቅና በመስጠት የለውጥ ሰራዊቱ የመሰረተ ልማት እና የአከባቢ ጥበቃ ማሻሻ ስራዎችን በመስራት ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባሮች በመታገል ፣ እና ልማታዊ መልካም አስተዳደርን በማስፈን እንዲወዳደሩ በማድረግ ለለውጥ እንዲተጉ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተሰርተዋል ፡፡ በተጨማሪም በየደረጃው ያሉትን አመራር ተገቢውን እውቀትና ክህሎት ባላቸውና የህዝብ ክንፉን በተገቢ ሁኔታ መምራትና ማነቃነቅ በሚችሉ አመራሮች የመተካት ስራ ከግዜ ወደ ግዜ በስፋት ተሰርል፡፡
3. የከተሞች የሥራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና
በመጀመሪያው GTP ለ 481 ማህበራት ለ 977 ወንድና ለ 535 ሴት በድምር ለ 1,512 አባላት በsሚ የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን ለነዚህ ማህበራት 3,417,831 ብር የብድር አገልግሎት ፤ 12,479.5M2 የማምረቻና መሸጫ የቦታ ድጋፍ ፤ 15,042,607 ብር የገበያ ትስስር እንዲሁም አጫጭር ስልጠናዎች በመስጠት ማህበራቱ ራሳቸውድ እንዲለውጡ የተደረገ ሲሆን ፤ በጊዛዊነት ለ663 ወንድ እና ለ203 ሴት በድምሩ ለ 866 ሰው የስራ እድል ተፈጥbል ፡፡ በሁለተኛ GTP ደግሞ 141 ማህበራት ለ 409 ወንድና ለ 495 ሴት በድምር ለ 904 አባላት በsሚ የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን ለነዚህ ማህበራት 830,000 ብር የብድር አገልግሎት ፤ 8752M2 የማምረቻና መሸጫ የቦታ ድጋፍ ፤ 12,594,515 ብር የገበያ ትስስር እንዲሁም አጫጭር ስልጠናዎች በመስጠት ማህበራቱ ራሳቸውድ እንዲለውጡ በመደረግ ላይ ይገኛል ፡፡ በተጨማሪ ለ 431 ወንድ እና ለ 119 ሴት በድምሩ ለ 540 ሰው በጊዛዊነት የስራ እድል መፍጠር ተችልዋል ፡፡
የከተሞች የልማታዊ መልካም አስተዳደር ስራዎች
የማዘጋጃ ቤታዊ አገሌግልት አሰጣጥ ስራዎች በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች በደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ ለ 5 ስራ አጥ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ ስራ እድል በመፍጠር እና 3 ማህበራት 13 ወንድ እና 4 ሴቶች በድምሩ 17 ስራ አጥ አባላት ያሉት በደረቅ ቆሻሻ ማንሳት በማደራጀት በከተማው የደረቅ ቆሻሻ ማንሳት ስራ ተሰርትዋል፡፡ እንዲሁም ሰፊ ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄን በመፍጠር ህብረተሰቡ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻን እነዲያስወግድ በመደረግ ላይ ይገኛል ፡፡ በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሩ ለደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ በማዘጋጀት እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻ ማሽን በማቅረብ ፍሳሽ ቆሻሻን በአግባብ እንዲወገድ እያደረገ ይገኛል ፡፡
የነዋሪዎች ተሳትፎና ንቅናቄ በከተሞች አገልግሎት አሰጣጥና የሰው ሀይል ልማት ላይ ያለው ተሞክሮ፡- የከተማዋ ነዋሪዎች በተለያዩ በ 1443 /አንድ ሺህ አራት መቶ አርቦ ሶስት/ 1፡5 የልማት ሰራዊት ፣ በ 285 /ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት/ የልማት ቡድን እና በተለያዩ የሴቶች የልማት ሰራዊት ፣ የወጣቶች ሊግ ፣ የሴቶች ሊግ እንዲሁም በተለያዩ ሲቪል ማህበራት የልማት አደረጃጀቶች በመደራጀት በከተማው አገልግሎት አሰጣጥ እንደ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት መስመር ዝርጋታ ፣ ደረቅ ቆሻሻ ማንሳት የፍሳሽ መውረጃ ቦዮችን ማፅዳት ላይ በንቃት በመሳተፍ በጣም መጠነ ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ ፡፡ ከነዚህ መካከል በከተማ አስተዳደሩ እና በማህበረሰብ አቀፍ ተሳትፎ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን በከተማው 93% ማድረስ ተችልዋል ፤ የፍሳሽ መውረጃ ቦዮችን በማፅዳት እና ተጨማሪ ውሃ መውረጃ ቦዮችን በመስራት የከተማውን ህብረተሰብ ከጎርፍ መታደግ ተችልዋል ፡፡ ነገር ግን የከተማው የገቢ አቅምና የማህበረሰቡ የመሰረተ ልማት ፍላጎት እንደ መንገድ ፣ መብራት እና ድልድይ ያሉት ባለመሙዋላታቸው በከተማው አገልግሎት አሰጣጥ ህብረተሰቡ ቅሬታ ያለው ቢሆንም ችግሩን በማህበረሰብ አቀፈ ተሳትፎ ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ ሌት ከቀን እየተጋ ይገኛል ፡፡
የከተማ ፕላን ፣ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ሪፎርም የከተማው ጠቅላላ መዋቅራዊ ፕላን በተመለከተ የከተማው ስፋት 1,598.33 ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለመኖሪያ ቤት ግንባታ 770.44 ሄክታር ፣ ለንግድ 71.41 ሄክታር ፣ ለአረንጉዋዴ ልማት እና ፓርክ 284.10 ሄክታር ፣ ለመንገድ ልማት 223.34 ሄክታር ፣ ለአስተዳደራዊና ማህበራዊ 120.62 ሄክታር ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት 179.72 ሄክታር እና ለሌሎች አገልግሎት 24.7 ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስት በአግባብ የለማው በመኖሪያ 183.2294 ሄክታር ፣ በንግድ 7.72 ሄክታር ፣ በአረንጉዋዴ ልማት እና ፓርክ 199.45 ሄክታር ፣ በመንገድ ልማት 85.22 ሄክታር ፣ በአስተዳደራዊና ማህበራዊ 103.21 ሄክታር እና ለሌሎች አገልግሎት 24.7 ሄክታር ነው ፡፡ በመኖሪያ ቤት ልማት በ 2007 ዓ.ም እና በ 2008 ዓ.ም አራት ዙር በተደረገ የመሬት ጫረታ 37 ቦታዎች 7,400m2 መሬት 1,592,425 ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን በተጨማሪም በንግድ ሁለት ቦታዎችን 330 m2 በጫረታ በማስተላለፍ 350,804 ብር ገቢ ማግኘት ተችለዋል፡፡ እንዲሁም በባክሎግ 140 ቦታዎች 28,000 m2 በማስተላለፍ 168,000 ብር ገቢ ተገኝትዋል ፡፡
የመኖሪያ ቤቶች ልማትና አስተዳደር
በዚህ ረገድ ከዚህ ቀደም በርከት ያሉ ስራዎች የተሰሩ ባይኖሩም በአሁኑ ወቅት የመኖሪያ ቤት አልባ የሆኑትን ማህበረሰቦች ክልሉ ባወጣው መመሪያ መሰረት አደራጅተን የጋራ መኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ ለመስጠት ከ ሶስት ሄክታር መሬት በላይ በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን ፡፡ በዚሁ መሰረት በተደራጀ መልኩ የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ የግንዛቤ እና ንቅናቄ መድረኮችን በመፈጠር ላይ እንገኛለን ፡፡ ከዚህ ባሻገር በከተማዋ ያሉ በአዋጅ 47/67 የተወረሱ 512 ቤቶች እና 155 በጋራ ቁጠባ የተሰሩ በድምሩ 667 ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ኪራይ በውል ተላልፈው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
የከተሞች የተቀናጀ መሰረተ ልማት አቅርቦት ስራዎች
የመሰረተ ልማት መስፋፋትን ተከትሎ የተፈጠሩ የስራ መስኮች በመጀመሪያው GTP ለ 221 ማህበራት ለ 977 ወንድና ለ 535 ሴት በድምር ለ 1512 አባላት 15,042,607 ብር የገበያ ትስስር የተፈጠረ ሲሆን በባለፈው አመት እና በ2009 ዓ.ም ደግሞ ለ 86 ማህበራት ለ 179 ወንድና ለ 82 ሴት በድምር ለ 261 አባላት 12,594,515 ብር የገበያ ትስስር ተፈጥbል፡፡ በዚሁ መሰረት በከተማው የተሰሩ መሰረተ ልማቶች 1.182 ኪሎ ሜትር ኮብልስቶን መንገድ፣ 19.3 ኪሎ ሜትር ጠጠር መንገድ ፣ 20 ሼዶች ፤ 1 ድልድይ ፣ 1.142 ኪሎ ሜትር የውሀ መውረጃ ቦይ ፣ 1 የ ከብት ተራ ፣ 2.1 ኪሎ ሜትር ከፍተኛ 33 KV እና 15.43 ዝቅተኛ 220/380V በድምር 17.53 ኪሎ ሜትር የመብራት መስመር ዝርጋታ ፣ 22 ኪሎ ሜትር የንፁህ ውሃ መጠጥ መስመር ዝርጋታ ፣ ቄራ ፣ መነሃሪያ እና የመሳሰሉት ናቸው ፡፡ በአካባቢ መሰረተ ልማት አቅርቦት ላይ የሕብረተሰቡ ተሳትፎን በተመለከተ በመጀመሪያው GTP የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ በመጠናከር ማህበረሰቡ በመሰረተ ልማት ግንባታ ከ 30-40% በገንዘብ እና በጉልበት እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ፡፡
የከተሞች የአረንጓዴ ልማትና የፅዳት ማሻሻያ ሥራዎች በከተማዋ የከተማ ፅዳትና አረንጓዴ ልማት ስራዎችን ለማሳካት በተለያዩ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን በመፍጠር ፣ በመድረክ ውይይት ፣ በሚኒ ሚድያ ጠዋትና ማታ ለማሀበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ፣ የቤት ለቤት ድጋፍ በመስጠት ማህበረሰቡ አከባቢውን እንዲያፀዳ በማድረግ እና የተለያዩ ለከተማ ውበትና አረንጉዋዴ ልማት የሚውሉ የዛፍ ችግኞችን አፍልቶ ለማህረሰቡ በማሰራጨት ከተማዋ ፅዱ ፣ ውብ እና ለነዋሪዎች ምቹ መኖሪያ እንድትሆን የተደራጀ የሕዝብ ንቅናቄ በመደረግ ላይ ይገኛል ፡፡ በዚህም ረገድ የተገኙ ለውጦች በጣም አበረታች እና ተስፋ ሰጪ ናቸው ፡፡
የከተማዋን ፅዳትና ውበት የሚያሳይ ፤ እንደ የመንገድ ላይ ዛፍ ፣ የችግኝ ጣቢያ ፣ መናፈሻ ቦታዎች ፣ ተቋማት…ወዘተ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች፣ የከተማዋ ገቢ(ፊይናንስ) ልማት የከተማዋ ገቢን በተመለከተ በመጀመሪያው "GTP" መጀመሪያዎች ከመሬት ልማት ጋር ተያያዥ የሆኑ ነገሮች እንደ መሬት አቅርቦትና ማስተላለፍ ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ /ካርታ/መስጠት ፣ ንብረት ማስተላለፍ የመሳሰሉት ታግደው በመቆየታቸው እና የገቢ መሰብሰቢያ ርእሶች በተገቢው ተለይተው የተሰራባቸው ባለመሆኑ ገቢው በአግባብ እየተሰበሰበ አልነበረም ፡፡ ነገር ግን ከ"GTP ው አጋማሽ በላ ሁሉንም የገቢ ርእሶች በተገቢው መልኩ ለይቶ በመሰብሰብ አበረታች ለውጦች እየታዩ መጥተዋል ፡፡ በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው "GTP" መጀመሪያ 1,846,081 ብር የነበረው አመታዊ ገቢ 2008 ዓ.ም ወደ 5,805,506.33 ብር ከፍ ማድረግ ተችልዋል ፡፡ በዚሁ ረገድ ሲያጋጥሙ የነበሩትን የካፒታል እጥረት ማህበረሰቡን በመሰረተ ልማት ግንባታ በገንዘብ ከ 30-40% በጉልበት እና በቁሳቁስ በንቃት በማሳተፍ እና የተገኘውን ገቢ በአማካይ ከ55-60% ለመሰረተ ልማት በማዋል ሲሰራ በመቆየቱ ብዙ አበረታች ለውጦችን ማስመዝገብ ተችልዋል ፡፡ የፊይናንስ አጠቃቀም በተመለከተ ተገቢውን የገቢና ወጪ ስርአትን በተከተለ መልኩ እና በየጊዝው ለማህበረሰቡ ይፋ በማድረግ ግልፅነትን በመፍጠር ነው ፡፡ ኢንቨስትመንት የከተማዋ የኢንቨስትመንት መስህቦች፣ ከተማዋ ለሰባት ወረዳዎች እና ለ አስራ አምስት አጎራባች ሰባት ወረዳዎች ውስጥ ላሉ ከተማዎች እንዲሁም ለባሌ ዞን መተላለፊያ እና አምስት መግቢያና መውጫ በሮች ያሉዋት በመሆንዋ ፣ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በ183 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በመገኘትዋ ምርትን በቅርበት ለአገር ውስትም ሆነ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ አመቺ በመሆንዋ እንዲሁም የምርት ግብአትንም ከውጪም ሆነ ከመሃል አገር በቀላሉ ለማቅረብ ምቹ በመሆንዋ ፤ ከተማዋ በወይናደጋ እና ለኢንቨስትመንት ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት ባለበት ቦታ ላይ የተመሰረተች በመሆንዋ ፤ ከተማዋ ለኢንቨስትመንት በቂና ምቹ እስትራክቸራል ፕላን የተሰራላት በመሆንዋ ፤ ከተማዋ ለኢንዱሰትሪ ግብአትና ግብይት አማራጭ የስንዴ ፣ ተልባና ጤፍ ምርት በስፋት የሚመረትበት አከባቢ በመሆንዋ ፤ ከተማዋ ለግንባታ የሚውሉ እንደ ነጭ እና ጥቁር ድንጋይ ፤ አሸዋና ቀይ አፈር ያሉ ግብአቶች መገኛ በመሆንዋ ፤ ከተማዋ መሰረተ ልማት እንደ የ 24 ሰዓት መብራት ፣ ውሃ ፣ የጠጠርና ኮብልስቶን መንገድ ፣ ተንቀሳቃሽ እና መደበኛ ስልክ እንዲሁም ማህበራዊ ተቁዋማት እንደ ሆስፒታል ፣ ጤና ጣቢያ ፣ ጤና ኬላዎች ፣ አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤቶች እና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተsማት የተሙዋሉላት በመሆንዋ የከተማ አስተዳደሩ ኑ በጋራ አርሲ ሮቤን እጅ ለአጅ ተያይዘን አናልማ በማለት ጥሪውን ሲያሥተላልፍ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0224430003፣ 0224430043 እና 0955013761 ይደውሉ በ ኢሜይል አድራሻ arsirobetownadmoff2017@gmail.com ይጠቀሙ ቱሪዝም/ባህል በከተማዋ ዙሪያ ያሉ የቱሪዝም መስህቦች ባሩዳ፣አቢናስ፣ሀርቡ እና ቱሉ ሻቶ ዋሻዎች፣ ፍንጫ ሮቤ ÷÷ቴ፣ አበርዳኝ ደን፣ ጉጃቤ ተራራ እንዲሁም ሼ አዛን እና አዮ ሞሚና የባህል ስፍራዎች ስላሉን ኑ የአረሲ ሮቤን ድንቅ የተፈጥሮና እና ሰው ሰራሽ ውብ መስህቦች እዩ የሮቤ ከተማ አስተዳደር መልእክት ነው፡፡
የከተማ አስተዳደሩ መልእክት እንደሚታወቀው በከተማ አስተዳደራችን ከመችውም ግዜ በላቀ ሁንታ በልማት ሰላም እና ዲሞክራሲ ዙሪያ አገራዊ መግባባትን በመፍጠር በመጀመሪያው የ "GTP" ምእራፍ ንቅቄ በመፍጠር በልማት ፣ ሰላምና ዲሞክራሲ ታላቅ እምረታን በማስመዝገብ በመጀመሪያው "GTP" ያሉትን ጉለቶችና ውስንነቶች በአግባቡ በመለየት እና የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎች በአግባብ በመቀመር የሁለተኛውን "GTP" እቅድ በማውጣት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብትዋል ፡፡ በዚሁ መሰረት የከተማ አስተዳደራችን የጀመረውን ዘርፈ ብዙ ጥረት በየደረጃው ያሉት የመንግስት መዋቅራት ፣ የዘርፉ ምሁራን ፣ ባለሃብቶች እና የከተማው ማህበረሰብ እንደተለመደው ከዚህ ቀደም ሲያደርገው የነበረውን ድጋፍ በማጠናከር በመሰረተ ልማት ግንባታ ፣ መልካም አስተዳደር ማስፈን ፣ ፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ማጥፋት ትግል ፣ አከባቢ ንፅህና አረንጉዋዴ ልማት ማሻሻያ ስራዎች ፣ በከተማው ዘላቂ ሰላም ማስፈን ስራዎች ፣ ለስራ አጦች የስራ እድል ፈጠራ እና ከተማዋን ወደ ኢንዱስትሪ ልማት የማሸጋገር ስራዎች እንዲሁም ከተማዋን ለህዝቦችዋ መኖሪያ አመቺ ፣ ምቹ እና ተስማሚ የማድረግ ተግባራት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም ጠንክረው እንዲሰሩ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ፡፡ በተጨማሪም በከተማው የምትገኙም ሆነ በሌላ አከባቢ የምትኖሩ የአከባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች እና ሙሁራን በከተማው ያሉትን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመጠቀም አብረን በጋራ እንስራ ፤ ከተማችንን ለማልማት በምናደርገው ጥረት ከጎናችን ቁሙ በጋራ የለማች ፅዱ አረንጉዋዴና ለመኖሪያም ሆነ ለስራ አመቺ የሆነች ሮቤን እንፍጠር እያልኩ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ ለአብሮነታችሁ አስቀድሜ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም በድጋሜ አመሰግናሁ፡፡